1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር በሀረሪ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 2014

ላለፉት ቀናት በሀረር ሲካሄድ የቆየው 1443 ኛው የሸዋል ኢድ በዓል ደማቅ እና አስደሳች መሆኑን የሀገር ውስጥ እና ከውጭ በበዓሉ የታደሙ አስተያየት ሰጭዎች ገለፁ። በዓሉ የሀረርን ቅርሶች ለማስተዋወቅ እና በተለያየ ምክንያት ተቀዛቅዞ ለቆየው ቱሪዝም መነቃቃት መፍጠሩን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/4B6HP
Äthiopien Stadt Harar | Shawwal Eid Feier
ምስል Mesay Tekilu/DW

 

ላለፉት ቀናት በሀረር ሲካሄድ የቆየው 1443 ኛው የሸዋል ኢድ በዓል ደማቅ እና አስደሳች መሆኑን የሀገር ውስጥ እና ከውጭ በበዓሉ የታደሙ አስተያየት ሰጭዎች ገለፁ። በዓሉ የሀረርን ቅርሶች ለማስተዋወቅ እና በተለያየ ምክንያት ተቀዛቅዞ ለቆየው ቱሪዝም መነቃቃት መፍጠሩን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል። የበዓሉ አከባበርም ተጠናቋል። በሀረሪ ክልል ለቀናት በተለያዩ መርሀ ግብሮች ሲከበር በቆየው የሸዋል ኢድ በዓል ላይ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት ትውልደ ኢትዮጵያዊ አቶ ካሊድ አብዱልዋሲ በዓሉ አንድነት እና ፍቅር የታየበት ደማቅ በዓል ሆኖ እንዳገኙት ገልፀዋል። 
የበዓሉ ታዳሚ የሆኑት ወ/ሪት ፈርዶሳ አቡበከር በበኩላቸው በሀገሪቱ የፀጥታ መደፍረስ ከሚታይባቸው አካባቢዎች በተለየ ሰላም ባለባት ሀረር በበዓሉ የታየው አብሮነት የሰላም እሴት  ለሌሎች አርአያ እንደሚሆን ገልፀዋል። የሀረሪ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ለ1443 ኛ ጊዜ የተከበረው የዘንድሮ ሸዋል ኢድ አጎራባች ክልሎች ተገኝተው ባህላቸውን ያስተዋወቁበት እና በጥቅሉ በዓሉ በድምቀት እና በስኬት የተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። 
ኃላፊው ሸዋል ኢድ በክልሉ ያሉ ቅርሶችን ከማስተዋወቅ ባለፈ በተለያየ ምክንያት ለተቃዛቀዘው ቱሪዝም መነቃቃት ፈጥሯል ብለዋል። "ከኢድ እስከ ኢድ" ወደ ሀገር ቤት መርሀ ግብር ጋር ተቀናጅቶ በተከበረው የሸዋል ኢድ በዛሬው እለት በተካሄደ ሲምፖዚየም በዓሉን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተደረገ ባለው ሂደት ዙርያ ምክክር ተካሂዷል።

መሳይ ተክሉ 


አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ