1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሐረር ከተማ የሸዋል ኢድ በዓል መከበር ጀመረ

እሑድ፣ ሚያዝያ 30 2014

በሀረር የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር ዛሬ ተጀምሯል። የሀረሪዎች ባህላዊ እሴት የሆነው ሸዋል ኢድ በሀገር አቀፍ ደረጃ "ከኢድ እስከ ኢድ" በሚል መርሀ ግብር ሲካሄድ ከቆየው ሀገራዊ ዝግጅት ጋር ተቀናጅቶ በድምቀት መከበሩ ሸዋልን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተካሄደ ላለው ጥረት አጋዥ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4AzVR
Äthiopien Stadt Harar | Shawwal Eid Feier
ምስል Messay Teklu/DW

በሐረር ከተማ የሸዋል ኢድ በዓል መከበር ጀመረ

በሀረር በየዓመቱ በኢድ አልፈጥር በዓል ሳምንት የሚከበረው የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር ዛሬ ተጀምሯል። የሀረሪዎች ባህላዊ እሴት የሆነው ሸዋል ኢድ በሀገር አቀፍ ደረጃ "ከኢድ እስከ ኢድ" በሚል መርሀ ግብር ሲካሄድ ከቆየው ሀገራዊ ዝግጅት ጋር ተቀናጅቶ በድምቀት መከበሩ ሸዋልን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተካሄደ ላለው ጥረት አጋዥ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር ተናግረዋል።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በበዓሉ ማስጀመርያ መርሀ ግብር ላይ እንዳሉት ሸዋል ኢድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ በቆየው "ከኢድ እስከ ኢድ" መርሀ ግብር ጋር መከበሩ የተለያየ ጠቀሜታ አለው።

Äthiopien Stadt Harar | Shawwal Eid Feier
ምስል Messay Teklu/DW

ርዕሰ-መስተዳድሩ "ከኢድ እስከ ኢድ" ወደ ሀገር ቤት መርሀ ግብር ተሰባስቦ በዓል ከማክበር ባለፈ በቱሪዝም ፣ በኢንቨስትመንት እና በሌሎች መስኮች ውጤት ለማምጣት እንደሚረዳ ጠቁመዋል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት የባህል እና ስፖርት ሚንስቴር ሚንስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ታሪካዊ ቅርሶቻችን እና ባህላችንን ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል ብለዋል።
"ከኢድ እስከ ኢድ" ወደ ሀገር ቤት መርሀ ግብር ጣምራ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በበኩላቸው ተከታዩን መልእክት አስተላልፈዋል።

በዛሬው የሸዋል ኢድ አከባበር መክፈቻ የቁሳቁስ ቅርስ ሀብቶችን የሚያስተዋውቅ የባህል ኤግዝቢሽን የተጀመረ ሲሆን ከምሽት ጀምሮ እስከ ማክሰኞ የሀረሪን ቅርስ እና ባህል የሚያስተዋውቁ የተለያዩ ዝግጅቶች ይከናወናሉ። 

መሳይ ተክሉ
እሸቴ በቀለ